Answers
ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው? ንስሓ የሚለው ቃል ከግዕዝ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን በአማርኛ ትርጓሜው ወይም የቃሉ ፍች እና ማብራሪያ፦ ማዘን፣ መፀፀት፣ መቆጨት፣ መቀጣት፣ ቀኖና መቀበል፣ ስለተሰራው ኀጢአት ካሳ መክፈል።፣ የሰሩትን በደል እና ጥፋት ማመን፣ አና በአጠቃላይ ማንኛውም ክርስቲያን ስለሰራው ኀጢአት ተፀፅቶ ወደ ፈጣሪው ሲመለስ የሚቀበለውን የቀኖና ንስሐ ያመለክታል። አንድ ክርስቲያን ንስሓ ለመግባት ተዘጋጀ ወይም ንስሓ ገባ ሲባል ማመኑን፣ መፀፀቱን፣ ወደ እግዚአብሔር መመለሱን፣ ክፉ ፀባዩን መተዉን፣ ከጥፋት ስራ መቆጠቡን እና መታረሙን የምናውቅበት መንገድ ነው። በተጨማሪም ንስሓ ማለት አንድ ክርስቲያን በሰራው ጥፋት በፈፀመው ኅጢያት እና ባደረገው ስህተት ሰለተፀፀተ እና ስለተቆረቆረ ሌላ ጊዜ ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላውን እና ሰማያዊ የዘላለም ህይወት ሊያሳጣው የሚችል ኀጢያትን ላለመፈፀም የመጨረሻ ውሳኔ የሚደርስበት የመደምደሚያ ሃሳብ ነው። በአጠቃላይ ንስሓ የቃሉ ማብራሪያ እና የጽንሰ ሃሳቡ ትንታኔ ከዚህ በላይ እንደተገለጸው ሲሆን፤ የንስሓን አስፈላጊነት በሚያምኑ ክርስቲያኖች ዘንድ የንስሓ ህይወት ያለውን ጠቀሜታ ስንመለከት የሚከተሉትን አቅጣጫዎች ይዞ እናገኘዋለን።